የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ደመቀ የኢትዮ-አሜሪካ  የባለ ብዙ ወገን ትብብር በተሟላ ሁኔታ እንዲተገበር ጠየቁ

By Mekoya Hailemariam

July 12, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) እየተሻሻለ የመጣውን የኢትዮ-አሜሪካ የሁለትዮሸና የባለ ብዙ ወገን ትብብር በተፋጠነና በተሟላ ሁኔታ ተግባራዊ መሆን እንዳለበት አቶ ደመቀ መኮንን ገለፁ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገረዋል::

በውይይታቸውም በሁለትዮሽና በወቅታዊው የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

እንዲሁም የሱዳን ሰላም የአፍሪካ ሕብረትና ኢጋድ መራሹ ሱዳናዊያን ባለቤት በሆኑበትና ሌሎች ተመሳሳይ ጥረት የተደገፈ ሊሆን እንደሚገባውም አቶ ደመቀ ገልጸዋል::

ሞሊ ፊ በበኩላቸው፥ ኢጋድ በአዲስ አበባ ያደረገውን ውይይት ኢትዮጽያ በማስተናገዷ አመስግነዋል።

የሱዳን ኃይሎችም የተኩስ አቁም በማድረግ ለችግሩ ፖለቲካዊ መፍተሄዎችን እንዲፈልጉና ሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽ እንዲያደርጉም አሳስበዋል::