Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ከተማ የ109 የአሰሪና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች የስራ ፈቃድ ተሰረዘ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ109 የአሰሪና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች የስራ ፈቃድ መሰረዙን የአዲስ አበባ የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡

እርምጃ የተሰወደባቸው ኤጀንሲዎች በሀገር ውስጥ ሰራተኞችን በማገናኘት ላይ የሚሰሩ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

የቢሮው የስራ እድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ፍስሀ ጥበቡ ዛሬ በሰጡት መግለጫ÷ ከኤጀንሲዎች የስራ ስምሪት ጋር በተያያዘ ከሕብረተሰቡ ቅሬታ ሲቀርብ መቆየቱን ተናግረዋል።

ቅሬታውን መሰረት በማድረግ ሰፊ የክትትል ስራ መከናወኑን በመግለጽ በዚህም ሕጋዊ አሰራር ሂደቶችን በመጣስ ሲሰሩ የነበሩ 109 የአሰሪና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች የስራ ፈቃድ እንዲሰረዝ ተደርጓል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

እርምጃ የተወሰደባቸው ኤጀንሲዎች የአሰሪና ሰራተኛ ቅጥር በሚመለከት የተቀመጠውን መስፈርት ሳያሟሉ አገልግሎት ሲሰጡ የተገኙ መሆናቸውንም ነው የተናገሩት፡፡

የመንግስትም ሆነ የግል ቀጣሪ ተቋማት ሰራተኞችን ከኤጀንሲዎች በሚቀጥሩበት ወቅት አስፈላጊውን ማጣራት እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.