Fana: At a Speed of Life!

የህዳሴ ግድብ በመጪው ክረምት ውሃ ለመያዝ የሚያስችለው ከፍታ ላይ ሰኔ ወር መጨረሻ እንዲደርስ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 24 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የግንባታ ቦታ የሚመለከታቸው የመንግስት፣ የተቋራጮችና አማካሪዎች የስራ ሀላፊዎች ጋር የስራ ግምገማና ጉብኝት ማድረጋቸውን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ገለፁ።

ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ ይህንንም ተከትሎ በትዊተር ገፃቸው እንዳሰፈሩት የግድቡ ግንባታ እየተፋጠነ እንደሚገኝ  በመግለፅ፥ በመጪው ክረምት የመጀመሪያ አመት ውሃ ለመያዝ የሚያስችለውን ዝቅተኛ ብሎክ ከ525 ሜትር ከፍታ ወደ 534 ሜትር ማደጉን አስታውቀዋል።

እሰከ ሰኔ ወር መጨረሻ ሳምንት 572 ሜትር እንዲደርስ እየተሰራ ይገኛልም ብለዋል።

ላለፉት አምስት ዓመታት 525 ሜትር ላይ ከነበረበት ወደሚፈለገው ደረጃ የማሳደጉ ስራ በቅርቡ የውሃ መያዝ የመቻላችን ጉዳይ ብርቱ ማሳያ መሆኑንም ነው ያመለከቱት።

ከዚህም ውጤት ለመድረስ ወደ ኋላ የሚመልሰን ነገር አይኖርም ያሉት ሚኒስትሩ፥ የብረት ስራዎች፣ የትላልቅ ውሃ ማስተላለፊያ በሮች ተከላ፣ የተርባይንና ጀነሬተሮች ተከላ እና ሌሎች ስራዎች በእቅድ እየተከናወኑ መሆኑን ገልፀዋል።

መፍጠን ያለባቸውን አስፈላጊ ስራዎች በመገምገም የማሻሻያ ውሳኔዎች መደረጋቸውን አመልክተዋል።

በግድቡ ግንባታ ስፍራም 24 ሰዓት እየተጉ ላሉ ባለሙያዎች ሚኒስትሩ ምስጋና አቅርበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.