Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ኬንያ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኖሩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ኬንያ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኖሩ፡፡

አቶ ደመቀ ነገ እና ከነገ በስቲያ በሚካሄደው 43ኛው የአፍሪካ ኅብረት የሥራ አሥፈጻሚ ምክር ቤት ስብስባ ላይ ለመሳተፍ ኬንያ ናይሮቢ መግባታቸው ይታወቃል።

አቶ ደመቀ መኮንን ዐሻራቸውን ያኖሩት ÷ በኬንያ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች እና ሰራተኞች ጋር ነው፡፡

የተተከለው ችግኝ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር አካል መሆኑን የኤምባሲው መረጃ ያመላክታል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሁለተኛውን ዙር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር “ነገን ዛሬ እንትከል” በሚል መሪ ሐሳብ በአፋር ክልል ማስጀመራቸው ይታወሳል።

በመርሐ-ግብሩም 25 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል ታቅዷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.