በአዲስ አበባ ከደረጃ በታች የሆኑ 12 ትምህርት ቤቶች ተዘጉ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከደረጃ በታች በሆኑ 12 ትምህርት ቤቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
ባለስልጣኑ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፥ በተሰጠው ተግባርና ሃላፊነት መሰረት የግል ት/ቤቶችን ለደረጃው በተቀመጠው መስፈርት መሰረት ለተቋማት ፍቃድና እድሳት እንደሚሰጥ አንስቷል፡፡
ተገቢውን ደረጃ ያላሟሉና የሕግ ጥሰት የፈጸሙ ተቋማት ላይ እርምጃ እንደሚወስድም ነው የገለጸው፡፡
በዚህ መሰረትም ለደረጃው የተቀመጠውን መስፈርት ያላሟሉ እና ከደረጃ በታች የሆኑ 12 ትምህርት ቤቶች የተዘጉ መሆኑን አስታውቋል፡፡
የተዘጉት ት/ቤቶችም አዲስ ተስፋ ቅድመ አንደኛ -አቃቂ፣ ዜድ ኤም ቅድመ አንደኛ-አቃቂ፣ ለግሎው ቅድመ አንደኛ -ንፋስ ስልክ፣ ኤልሻዳይ ቅድመ አንደኛ -ንፋስ ስልክ፣ ቆሬ ብርሃን ቅድመ አንደኛ -ንፋስ ስልክ፣ማይድሪምላንድ ቅድመ አንደኛ-ንፋስ ስልክ፣ ቲ ፒ ፋይ ቅድመ አንደኛ -ንፋስ ስልክ፣ሮማናት ቅድመ አንደኛ -ንፋስ ስልክ፣ አዲስ ቪዥን ቅድመ አንደኛ ቦሌ፣ አዲስ ቪዥን የመጀመሪያ ደረጃ- ቦሌ፣ ኢልመኑር ቅድመ አንደኛ -ኮልፌ ቀራንዮ፣ ስትራይቨርስ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት-ንፋስ ስልክ ናቸው፡፡
ትምህርት ቤቶቹ ለ2016 ዓ.ም ማስተማር የማይችሉ መሆኑን የገለጸው ባለስልጣኑ÷ የተማሪዎችን ውጤት የሚገልጽ መረጃ ለተማሪዎችና እውቅና ፍቃድ ለሰጣቸው አካል እንዲያስረክቡ አሳስቧል፡፡