Fana: At a Speed of Life!

የሳንባ ካንሰር ዋና ዋና አጋላጭ ሁኔታዎች ምንድንናቸው?

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሳንባ ካንሰር ማለት በሳንባ ውስጥ የሚገኙ ህዋሳት ከመደበኛ ዕድገታቸውና ቁጥራቸው ውጪ ጤናማ ባልሆነ መልኩ መባዛት ነው፡፡

የሳንባ ካንሰር ከሳንባ ተነስቶ ወደ አንጎል እንዲሁም ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ሊሰራጭ እንደሚችል የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

ታዲያ የሳንባ ካንሰር ዋና ዋና አጋላጭ ሁኔታዎች ምንድናቸው?

-ማጨስ፡- ማጨስ ለሳንባ ካንሰር ዋነኛ አጋላጭ ሁኔታ ሲሆን፥ የትምባሆ ምርቶችን መጠቀም ለሳንባ ካንሰር የመጋለጥ ዕድልን ይጨምራል፡፡

ማንኛውም የዕድሜ ክልል ማጨስን ማቆም በሳንባ ካንሰር የመጋለጥ ዕድልን ሊቀንስ ይችላል፡፡

-የስራ ቦታ፡- በብዛት ከሚታወቁ የስራ ቦታ አጋላጭ ሁኔታዎች ውስጥ እንደ አስቤስቶስ፣ ሲሊካ፣ ራዶን፣ ከባድ ብረቶች፣ ፖሊሳይክሊክ እና ሃይድሮካርቦን የመሳሰሉ ኬሚካሎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡

– የአየር ብክለት፡- በቤት ውስጥ እንዲሁም ከቤት ውጪ የሚኖር የአየር ብክለት ለሳንባ ካንሰር ተጋላጭ ያደርጋል፡፡

በተለይም በቂ አየር በሌላቸው ቤቶች ውስጥ ከሰል፣ እንጨት እና ሌሎች ለማገዶ የምንጠቀማቸው ነገሮች የሚያወጡት ጭስ ሴቶችን ይበልጥ ተጋላጭ እንደሚያደርጋቸው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

– የቤተሰብ ሁኔታ፡- የሳንባ ካንሰር በቤተሰብ ውስጥ በዘር የመተላለፍ ዕድሉ ከፍ ያለ መሆኑን የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

– የጨረር ህክምና፡- በተደጋጋሚ በደረት ላይ የሚደረግ የጨረር ምርመራ በሳንባ ካንሰር የመጋለጥ ዕድልን ከፍ ያደርጋል፡፡

በመሆኑም ከላይ የተዘረዘሩትን አጋላጭ ሁኔታዎች መቀነስ ወይም ማስወገድ የሳንባ ካንሰርን ለመከላከል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ባለሙያዎቹ ይመክራሉ፡፡

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.