የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት በሐረር ከተማ ያስገነባው የዳቦና ዱቄት ፋብሪካ ተመረቀ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት በሐረር ከተማ ያስገነባው 7ኛው የዳቦና ዱቄት ፋብሪካ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ፡፡
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽታያቸውን ጨምሮ የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሚስራ አብደላና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
ፋብሪካው በቀን 300 ሺህ ዳቦና 420 ኩንታል ዱቄት ያመርታል መባሉን የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
በሶስት ፈረቃ ከ150 በላይ ለሆኑ ሰዎች የስራ እድል መፍጠሩም ተመላክቷል፡፡
በቀጣይም በአምስት ከተሞች እየተገነቡ ያሉ ፋብሪካዎች ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆኑ ግንባታቸው እየተፋጠነ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
በከዲሪ ሸምሰዲን