Fana: At a Speed of Life!

በአለም ዙሪያ ከ50 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ በከባድ ፅኑ ህመም  ውስጥ ይገኛሉ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 25 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአለም ከ50 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ በከባድ ፅኑ ህመም ውስጥ ይገኛሉ፡፡

የኮሮና ቫይረስ ከተከሰተ ወራትን ሲያስቆጥር 212 ሃገራትን አዳርሷል።

እስካሁንም በዓለም 3 ሚሊየን 485 ሺህ 936 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ፥ 244 ሺህ 380 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

50 ሺህ 863 ሰዎች ደግሞ በፅኑ ታመው በከባድ ሁኔታ ውስጥ ናቸው፡፡

እንደ ጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ በአሜሪካ 1ሚሊየን 133 ሺህ 69 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 67 ሺህ 448 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል፤ በዚህም ከአለም በአንደኝነት ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡

በሃገሪቱ 175 ሺህ 382 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።

በስፔን 216 ሺህ 582 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 117 ሺህ 248 ሰዎች ማገገም ችለዋል።

እንዲሁም በጣሊያን 209 ሺህ 328 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ፥  79 ሺህ 914 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በብሪታኒያ 183 ሺህ 500 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 901 የሚሆኑት ሰዎች ከቫይረሱ ማገገም ችለዋል።

በአፍሪካ እስካሁን ከ41 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ  1 ሺህ 721 ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት ተዳርገዋል። 13 ሺህ 760 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.