Fana: At a Speed of Life!

በኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ (ኢ/ር) የተመራ ልዑክ ከፖርቹጋል የሥራ ሀላፊዎች ጋር ውይይት አካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ (ኢ/ር) የተመራ ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች ልዑክ ከፖርቹጋል የጫማ አምራቾች ማህበር እና የጨርቃ ጨርቅ እንዲሁም ጋርመንት ማህበር ፕሬዚዳንቶች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

በፖርቹጋል ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረገ የሚገኘው የኮሚሽኑ ልዑክ በንግድ ከተማነቷ በምትታወቀው ፖርቶ ከተማ በመገኘት ነው ከስራ ሀላፊዎቹ ጋር ውይይት ያካሄደው፡፡

ቡድኑ በሀገሪቱ ከሚገኙ የተለያዩ ዘርፍ ሃላፊዎች ጋር በመገናኘት ምክክር ማካሄዱ ተገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ የውጭ ኢንቨስትመንት ሴክተሮች በተለይም በቆዳ እና ጨርቃ ጨርቅ ዘርፎች ላይ መሰማራት የሚያስገኛቸውን ጥቅሞች ለሥራ ሀላፊዎቹ ገለጻ መደረጉም ተጠቅሷል፡፡

ቡድኑ በፖሊሲ እና በኢንቨስትመንት መሰረተ ልማቶች ላይ ስለተሰሩ ስራዎች እንዲሁም በመንግስት ስለተደረጉ ማሻሻዎች ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

መንግስት ዘርፉን ለመደገፍ ጠንካራ አቋም እንዳለውም ቡድኑ ማረጋገጡን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

የፖርቹጋል የዘርፉ ሃላፊዎችም የኢትዮጵያን የኢንቨትመንት ዕድሎች እና አማራጮችን ለመቃኘት ፍላጎት እንዳላቸው እንዲሁም በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.