ስፓርት

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2016 ዓ.ም ውድድር መስከረም 20 ይጀመራል

By Melaku Gedif

July 13, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር የ2016 ዓ.ም ውድድር መስከረም 20 ቀን እንደሚጀመር አስታውቋል፡፡

የ2015 ዓ.ም ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ሐምሌ 1 ቀን 2015 ዓ.ም መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡

በቀጣይ የሚካሄደው የ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርም መስከረም 20 ቀን 2016 ዓ.ም እንዲጀመር መወሰኑን የአክሲዮን ማህበሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

የውድድር ዘመኑ  የሚጀምርበትን ቀን ተሳታፊ ክለቦች  እንዲያውቁ መደረጉ ተጠቁሟል፡፡