Fana: At a Speed of Life!

ሉሲዎቹ የቻድ አቻቸውን 6 ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የቻድ አቻውን 6 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

በ2024 ኦሊምፒክ የሴቶች እግር ኳስ የአፍሪካ ዞን የመጀመርያ ዙር ማጣሪያ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከቻድ አቻው ጋር ጨዋታውን አድርጓል፡፡

በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሉሲዎቹ የጨዋታ የበላይነት በመውሰድ 6 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ አጠናቋል።

በዚህም መሳይ ተመስገን በ13ኛው ደቂቃ የመጀመሪያዋን ግብ ፣ አረጋሽ ካልሳ ሁለተኛውን እና 4ኛውን ግብ በ24ኛው እና በ63ኛው ደቂቃ፣ ሦስተኛውን ግብ ናርዶስ ጌትነት በ36ኛው ደቂቃ፣ አምስተኛውን ረድዔት አስረሳኽኝ በ79ኛው ደቂቃ እንዲሁም 6ኛውን ንቦኝ የን በ82ኛው ደቂቃ አስቆጥረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.