ስፓርት

የ2026 የዓለም ዋንጫ የአፍሪካ ዞን ማጣሪያ የምድብ ድልድል ይፋ ሆነ

By Shambel Mihret

July 13, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2026 የዓለም ዋንጫ የአፍሪካ ዞን ማጣሪያ የምድብ ድልድል ኢትዮጵያ ከግብፅ፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ጊኒ ቢሳው፣ ሴራ ሊዮንና ጅቡቲ ጋር ተደልድላለች፡፡

የ2026 ዓለም ዋንጫ የአፍሪካ ዞን ማጣርያ የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓት በኮትዲቯር አቢጃን ተካሂዷል፡፡

በዚህም ኢትዮጵያ በምድብ ሀ ከግብፅ፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ጊኒ ቢሳው፣ ሴራ ሊዮን እና ጅቡቲ ጋር መደልደሏን ከእግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡