የጥርሳችንን ጤና እንዴት እንጠብቅ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጥርስዎን በቀን ሁለት ጊዜ ማለትም ጠዋትና ማታ በመቦረሽ የጥርስዎን ጤንነት መጠበቅ ይገባል፡፡
ጥርስን በትክክለኛው መንገድ መቦረሽ ንፅህናው እንዲጠበቅ እንዲሁም መቦርቦር እና ሌሎች የጥርስ ችግሮችን ማስወገድ እንደሚያስችል የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡
ጥርስዎን በትክክለኛው መንገድ ሲቦርሹ፣ ጥርሶችዎ ንፁህ ይሆናሉ፣ ይህም ለአፍ ጤንነት አስፈላጊ ነው።
ታዲያ ትክክለኛው የጥርስ አቦራረሽ ምን ይመስላል?
-ጥርስ ብሩሽን ከድዳችን መስመር በ45° በመያዝ መቦረሽ
– በዝግታ እና በአጭሩ የጥርስ ብሩሽን በጥርሳችን አካባቢ ወደፊት እና ወደኋላ ማንቀሳቀስ
-ከዚያም ክብ በመስራት፣ ወደላይና ወደታች፣ የጥርሳችንን ውስጥ፣ በማላመጫቻችን በኩል የጥርሳችን ክፍል ሁሉንም ጥርሶች መቦረሽ፡፡
-ጥርሳችንን ቦርሸን ከጨረስን በኋላ ባክቴሪያዎችን እና መጥፎ የአፍ ጠረንን ለማስወገድ ምላሳችንን መፋቅ ይኖርብናል፡፡
በመጨረሻም አፋችንን በመደጋገም በውሃ መጉመጥመጥ ናቸው፡፡
ከመጠን በላይ መቦረሽ ተገቢ አለመሆኑን እና በሀይል መቦረሽ በጥርስ እና በድድ ላይ ጉዳት እንደሚያስከትል ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡