Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ ከሩሲያ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 7 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ ከሩሲያ አምባሳደር ዬቭጌኒ ተርክሂን ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

የሩሲያ ከተሞች ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር የሚኖራቸውን ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው የትብብር መንገዶች ዙሪያ በስፋት መክረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.