Fana: At a Speed of Life!

ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ያሰለጠናቸውን የፖሊስ መኮንኖች አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 8 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሐ ግብሮች ያሰለጠናቸውን የፖሊስ መኮንኖች አስመርቋል።

 

ሰልጣኞቹ በፖሊሰ ሳይንስ፣ በሥነ – ወንጀልና ወንጀል ፍትሕ እንዲሁም በፖሊስ መኮንንነት ዘርፍ ከሰርተፊኬት እስከ ሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።

 

ከተመራቂዎቹ መካከል በተለያዩ ክልሎች ከዚህ ቀደም በልዩ ሀይል አባል የነበሩ የፌዴራል ፖሊስን ለመቀላቀል የመረጡ  ስልጠናቸውን ተከታትለው በዛሬው የምረቃ ሥነ ስርዓት እንደሚገኙበት ተገልጿል ።

 

በዛሬው እለት ለምርቃት የበቁት 623 የፖሊስ መኮንኖች ናቸው።

 

በበረከት ተካልኝ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.