Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል185 ሺህ ኩንታል ማዳበሪያና ምርጥ ዘር ለአርሶ አደሮች ተከፋፈለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል ለ2015/2016 የምርት ዘመን በግብዓትነት የሚውል 185 ሺህ ኩንታል ማዳበሪያና ምርጥ ዘር ለአርሶ አደሮች መከፋፈሉ ተገለጸ ።

የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የእርሻና ገጠር ልማት ቢሮ የአዝርእትና አፈር ልማት ዳይሬክተር ሰለሞን ገብረ ሥላሴ እንደገለጹት፥ ለአርሶ አደሮች ከተከፋፈለው ውስጥ 148 ሺህ ኩንታል ማዳበሪ ከፌዴራል መንግስት የተላከ ነው።

እንዲሁም 37 ሺህ ኩንታል የጤፍ ምርጥ ዘር ለአርሶ አደሮች በነጻ መከፋፈሉን ነው ለኢዜአ የተናገሩት፡፡

ምርጥ ዘሩ ከኦሮሚያ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልሎች እና ከግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ የተገኘ ነው ብለዋል፡፡

ከኦሮሚያ ክልል በድጋፍ የተገኙን 30 ትራክተሮች በክልሉ ከነበሩ 39 ትራክተሮች ጋር በማቀናጀት 150 ሺህ ሄክታር በኩታ ገጠም እየለማ ይገኛል ነው ያሉት፡፡

በምርት ዘመኑ 1 ነጥብ 3 ሚሊየን ሄክታር በተለያዩ ሰብሎች ለማልማት ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ለአርሶ አደሮች ከተከፋፈለው የአፈር ማዳበሪያ በተጨማሪም አርሶ አደሮች የተፈጥሮ ማዳበሪያ አዘጋጅተው ጥቅም ላይ እያዋሉ መሆኑን አስረድተዋል፡፡፡

በክልሉ በ2015/16 ምርት ዘመን ለማልማት ከታቀደው መሬት 17 ሚሊየን ኩንታል ምርት ይገኛል ይጠበቃል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.