በጋምቤላ ክልል የአንድ ጀምበር አረንጓዴ አሻራን የማሳረፍ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል የአንድ ጀምበር አረንጓዴ አሻራን የማሳረፍ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።
በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄደ ባለው የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በችግኝ ተከላው እየተሳተፉ መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉን ጨምሮ የፌዴራል፣ የክልልና የጋምቤላ ከተማ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በመሳተፍ ላይ ናቸው።