የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የአየር ንብረት ለውጥን ለመታገል የተግባር ማሳያ ነው – ኦሬሊያ ቻሌብሮ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ከወሬ ባለፈ የአየር ንብረት ለውጥን በተግባር ለመታገል ዋና ማሳያ ነው ሲሉ በተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ኦሬሊያ ቻሌብሮ ተናገሩ፡፡
በተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት በኢትዮጵያ አንድ ጀንበር 500 ሚሊየን ችግኞች ተከላ መርሐ ግብር ላይ ተሳትፏል፡፡
በድርጅቱ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ኦሬሊያ ቻሌብሮ ባስተላለፉት መልዕክት “በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ ከንፈርን ከመምጠጥ ባለፈ ለዓለም በተግባር ያሳየችበት ነው” ብለዋል፡፡
በአንድ ጀንበር 500 ሚሊየን ችግኞች ተከላ መርሐ ግብር ላይ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች እና ሰራተኞች ተሳትፈዋል፡፡