Fana: At a Speed of Life!

የፌዴራል ፖሊስ አባላት 500 ሚሊየን ችግኝ በአንድ ጀንበር የመትከል መርሐ ግብር ላይ ተሳተፉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አመራሮች እና አባላት በአንድ ጀንበር 500 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሐ ግብር ላይ ተሳትፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አመራር እና አባላት በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 7 እንዲሁም የፖሊስ ሰራዊቱ በሚገኙባቸው የተለያዩ አካባቢዎች ነው አረንጓዴ አሻራቸውን ያኖሩት፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል÷ ተቋማቸው የኢትዮጵያን ሰላም እና ደህንነት ከማስከበር ጎን ለጎን በየትኛውም የልማት ተሳትፎ ከፍተኛ ድርሻ እየተወጣ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በዛሬው ዕለትም የፌዴራል ፖሊስ አባላት በተሰማሩባቸው የተለያዩ አካባቢዎች ችግኝ መትከላቸውን አንስተዋል፡፡

የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር  አየር ንብረትን በመጠበቅ ረገድ  ሚናው ከፍተኛ ነው ያሉት ከሚሽነር ጀኔራሉ ÷መርሐ ግብሩ ቀጥዩ ትውልድ የተሻለች ኢትዮጵያን የሚያይበትን ዕድል ይፈጠራል ብለዋል፡፡

በዛሬው ዕለት በፖሊስ አባላት ለተተከሉ ችግኞች ጥበቃ እና ክትትል ይደረጋል ማለታቸውንም የፌዴራል ፖሊስ  መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.