Fana: At a Speed of Life!

ከጥራት ደረጃ በታች የሆኑ ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ታገዱ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከጥራት ደረጃ በታች የሆኑ ከ2 ሺህ 500 ሜትሪክ ቶን በላይ ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ መታገዱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባለፉት 9 ወራት አስገዳጅ የኢትዮጵያ ደረጃ የወጣላቸው የገቢ ምርቶች ላይ ባካሄደው የጥራት ቁጥጥር ከ2 ሺህ 500 ሜትሪክ ቶን በላይ የሚሆኑት ከደረጃ በታች በመሆናቸው ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ታግደዋል።

ከታገዱት የገቢ ምርቶች ውስጥ 2 ሺህ 304 ነጥብ 9 ሜትሪክ ቶን ጥቅል ብረት፣ 28 ነጥብ 7 ሜትሪክ ቶን የቤት ክዳን ቆርቆሮ፣ 180 ካርቶን ሳሙና፣ 142 ካርቶን በፀሐይ ብርሀን የሚሰራ የእጅ ባትሪ፣ 150 ካርቶን የኤሌክትሪክ ገመድ እንዲሁም 43 ነጥብ 2 ሜትሪክ ቶን የቆርቆሮ መስሪያ ጥሬ እቃ ይገኙበታል።

በተጨማሪም 272 ጥቅል የአርማታ ብረት፣ 19 ሺህ 770 ጀሪካን ፓልም የምግብ ዘይት፣ 2 ሺህ 934 ፍሬ የውሃ ፓምፕ፣ 875 ካርቶን ባትሪ ድንጋይ እንዲሁም የታሸጉ ምግቦችና ሌሎችም የገቢ ምርቶች በቁጥጥሩ ወቅት ከጥራት መስፈርት በታች ሆነው በመገኘታቸው ወደ ሀገር ውስጥ ገበያ እንዳይገቡ ተደርገዋል ነው ያለው።

በዚህም  በህብረተሰቡ ላይ የሚያደርሱትን የጤና፣ የደህንነትና የጥቅም ጉዳት ማስቀረት መቻሉን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.