Fana: At a Speed of Life!

በሀገራት መካከል ያለውን የበይነ-መረብ ተደራሽነት ክፍተትን መሙላት ቀዳሚ አጀንዳ መሆን አለበት ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ባደጉ እና በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት መካከል ያለውን የበይነ-መረብ ተደራሽነት ክፍተትን መሙላት ቀዳሚ አጀንዳ መሆን እንዳለበት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ዓለም አቀፉ የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባዔ ከፍተኛ መሪዎች ጉባዔው ማተኮር በሚገባው አጀንዳ ዙሪያ በስዊዘርላንድ ጄኔቭ መክረዋል።

ዓለም አቀፉ የነይነ መረብ አስተዳደር ጉባዔ በሃገራት መካከል ያለውን የበይነ-መረብ ተደራሽነት ክፍተት መሙላት ቀዳሚ አጀንዳ ማድረግ እንደሚገባው በውይይቱ ወቅት ተጠቁሟል።

የጉባዔው የከፍተኛ መሪዎች አባልና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴዔታ ሁሪያ አሊ፥ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት የበይነ-መረብ ተደራሽነት፣ መሰረተ ልማትና የዲጂታል መጠቀሚያ መሳሪያዎች እጥረት የጉባዔው አጀንዳዎች መሆን እንደሚገባቸው ተናግረዋል።

ለሀገራት የኢኮኖሚ እድገት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ጠቅሰው፥ ይህንን ከግብ ለማድረስ የዲጂታል ማህበረሰብ መፍጠር ላይ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የጉባዔው ከፍተኛ መሪዎች ዓለም አቀፉ የበይነ መረብ አስተዳደር ጉባዔ መጠናከር በሚችልበትና ከተለያዩ ተቋማት ጋር በጋራ መስራት በሚችልበት አግባብ ዙሪያ ምክክር መካሄዱን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.