Fana: At a Speed of Life!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የባህል ሙዚየም ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለሚገነባው የባህል ሙዚየም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን የመሠረት ድንጋይ አስቀመጡ፡፡

አቶ አሻድሊ ሀሰን በዚሁ ወቅት÷የባህል ሙዚየሙ ዲዛይን የክልሉን አጠቃላይ ገጽታ በሚያሣይ መልኩ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

በክልሉ እስካሁን ከመደመር ትውልድ መጽሐፍ ከ42 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሠብሰቡንም ገልጸዋል።

በክልሉ ሊተዋወቁ የሚገባቸው ታሪኮች፣ ባህላዊ እሴቶች፣ ተፈጥሯዊና ሠው ሠራሽ የቱሪዝም ሃብቶች እንዳሉም ጠቁመዋል፡፡

ለሀብቶቹ መተዋወቅ የሙዚየሙ መንባት ወሣኝ ሚና እንዳለውም ማስረዳታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሲጠናቀቅ ለክልሉ ይዞት የሚመጣው የቱሪዝም እንቅስቃሴ ከፍተኛ መሆኑንም አቶ አሻድሊ ጠቅሰዋል፡፡

ለዚህም ሙዚየሙ ደረጃውን በጠበቀ መንገድ በአጭር ጊዜ ተገንብቶ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ሁሉ ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል።

‘የመደመር ትውልድ መጽሐፍ’ በክልሉ በሚኖረው ሽያጭ የሚገኘው ገቢ የክልሉን ባህላዊና ታሪካዊ ዕሴቶች የሚያንጸባርቅ ደረጃውን የጠበቀ የባህል ሙዚዬም ለመገንባት እንዲውል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ መስጠታቸው ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.