ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለአምባሳደር ሙሀሙድ ድሪር የክብር ዶክትሬት ሰጠ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ዩኒቨርሰቲ 1 ሺ 211 ተማሪዎችን አስመርቋል።
ከተመረቁት ተማሪዎች መካከል 382ቱ ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል።
ተመራቂዎቹ 248 በድህረ ምረቃ እንዲሁም 963ቱ በቅድመ ምረቃ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ናቸው ተብሏል።
የዘንድሮ ምረቃ የመውጫ ፈተና ከተሰጠበት ማግስት መሆኑ ለየት እንደሚያደርገው ÷ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዑባህ አደም (ዶ/ር) አስታውቀዋል።
የመውጫ ፈተናውን ከወሰዱት የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች መካከል 56 በመቶው ፈተናውን ማለፋቸውን ገልፀዋል።
ዩኒቨርሲቲው ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሙሀሙድ ድሪር የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል።
አምባሳደር ሙሀሙድ ድሪርም ለተመራቂዎቹ የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።
በምረቃ ሥነ ሥርአቱ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡኽን ጨምሮ የተመራቂ ተማሪ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።
በእዮናዳብ አንዱዓለም