Fana: At a Speed of Life!

ዶክተር ፍፁም አሰፋ ከግሎባል ግሪን ግሮውዝ ተወካይ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) ከግሎባል ግሪን ግሮውዝ የኢትዮጵያ ተወካይ ሚስተር ዳንኤል ኦግቦንያ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸው ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ተጽዕኖን ለመቋቋም የወሰደቻቸውን የፖለቲካ ቁርጠኝነት እና የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በተመለከተ ሚኒስትሯ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ከሀገራዊ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች እና ዕቅዶች ጋር በተጣጣመ መልኩ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ጨምሮ የተለያዩ ተግባር ተኮር ስራዎች በመተግበር ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል።

የግሎባል ግሪን ግሮውዝ የኢትዮጵያ ተወካይ ሚስተር ዳንኤል ኦግቦንያ በበኩላቸው÷ ድርጅታቸው ኢትዮጵያ ለምታደርጋቸው የአየር ንብረት ለውጥ ተግባራት የሚያደርገውን ድጋፍ  አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

በውይይቱ የፕላን እና ልማት ሚኒስትር በግለባል ግሪን ግሮውዝ አባል ሀገራት የተቀመጠውን ዝቀተኛ የካርቦን ልቀት ስትራቴጂ ተግባራዊ እንዲያደርግ ስምምነት ላይ መደረሱን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.