Fana: At a Speed of Life!

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከ3 ድርጅቶች ጋር ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን እውን ለማድረግ የሚያስችል የጋራ ግብረ ኃይል ለማቋቋም ከሦስት ድርጅቶች ጋር  ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

ድርጅቶቹ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ፣ ሱሚቶሞ ኮርፖሬሽን እና የጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ጃይካ)  ናቸው፡፡

ስምምነቱም የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 መርሐ- ግብርን ለማጠናከር ያለመ ስለመሆኑ የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር )በስምምነቱ ላይ እንደገለጹት÷  የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 መርሀ-ግብርን እውን ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር  በትብብር እየተሰራ  ነው፡፡

የዚህ ስትራቴጂያዊ አጋርነት ትግበራ በዲጂታል መሠረተ ልማቶች፣  የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶችን ማሻሻል፣ የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓቶች እና የሳይበር ደኅንነት ትብብርን እንደሚያጠቃልል አብራርተዋል፡፡

የሦስቱ ድርጅቶች ፕሬዚዳንቶች በበኩላቸው÷ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 መርሐ-ግብርን እውን ለማድረግ በተፈረመው ስምምነት መሰረት ከሚኒስቴሩ ጋር በጋራ እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል፡፡

የሚቋቋመው ግብረ-ኃይልም የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን ውጤታማ በሆነ መንገድ በመጠቀም የዘርፉን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ ይሸራል መባሉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.