አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ረዳት ዋና ፀሀፊ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 13 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ረዳት ዋና ፀሀፊ ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይታቸው በሰብአዊ ጉዳዮች ላይ በትብብር መስራት በሚቻልበት አግባብ ላይ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
በተጨማሪም ከተባበሩት መንግስታት የሰላም ስራዎች ምክትል ዋና ጸሃፊ ጃን ፒየር ላክሮዊክስ ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ምክክር አድርገዋል፡፡
በዚህ ወቅትም በሰላም ጉዳዮች ላይ በትብብር መስራ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።