ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ጋር በስልክ ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 13 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ ጋር ተወያዩ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ፥ ከፕሬዚዳንቱ ጋር በሁለትዮሽ እና በዓለም አቀፍ የጋራ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን አስታውቀዋል።
በተጨማሪም በዩክሬን እና በሩሲያ መካከል ሰላም ማምጣት በሚቻልበት መንገድ ላይ በስልክ ተወያይተናል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።