Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አሜሪካ በረራ የጀመረበት 25ኛ ዓመት ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አሜሪካ የሚያደርገውን በረራ የጀመረበት 25ኛ ዓመት አክብሯል።

በስነስርዓቱ ላይ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ.ር ኢንጂነር) ተገኝተዋል።

በአሜሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ እንዳሰፈረው፥ አየር መንገዱ ከ25 ዓመታት በፊት ወደ አሜሪካ በረራ መጀመሩን ጠቅሷል።

አየር መንገዱ ከ25 ዓመታት በፊት ወደ አሜሪካ በረራ መጀመሩ የሁለቱን አገሮች ግንኙነት ለማጠናከር የራሱን ሚና መጫወቱን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያወጣው መረጃ ጠቁሟል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.