Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከፓኪስታን አቻቸው ጋር በስልክ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ከኻን ጋር በስልክ ተወያዩ።

መሪዎቹ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በአዳጊ ሀገራት ላይ እያሳደረ ባለው አሉታዊ ተፅእኖ ዙሪያ መክረዋል።

በውይይታቸውም የቫይረሱ ወረርሽኝ በኢኮኖሚ ላይ የሚኖረውን አሉታዊ ተፅእኖ ለመግታት ለአዳጊ ሀገራት እዳ ስረዛ እንደሚያስፈልጋቸው ከስምምነት ደርሰዋል።

ሀገራቱ ኢኮኖሚያቸው ከኮሮና ቫይረስ እስከሚያገግም ድረስ በጋራ እንሰራለን ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የኮቪድ-19 ኢትዮጵያን በመሰሉ አዳጊ ሀገራት ኢኮኖሚ ላይ እያሳደረ ያለው ዘርፈ ብዙ ችግርን በማንሳት አበዳሪ ሀገራት እና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት ብድር በመሰረዝ የሀገራቱን ኢኮኖሚ መታደግ ይገባቸዋል ባይ ናቸው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.