Fana: At a Speed of Life!

አንጋፋው አጥቂ ሳላዲን ሰዒድ ጫማ ሰቀለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ክለቦች እና በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለበርካታ አመታት አገልግሎት የሰጠው ሳላዲን ሰዒድ ጫማውን ሰቅሏል፡፡

ሳላዲን ሰይድ ለ15 ዓመታት በብሔራዊ ቡድን እና እና በተለያዩ ክለቦች መጫዎት የቻለ ሲሆን በ37 ዓመቱ ጫማ መስቀሉን ለሶከር ኢትዮጵያ አስታውቋል፡፡

አጥቂው በ2014/15 የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ የውድድር ዘመንም ከሲዳማ ቡና ጋር ድንቅ ጊዜን ማሳለፍ ችሏል፡፡

ሳላዲን በተጫዋችነት ዘመኑ በሙገር ስሚንቶ፣ቅዱስ ጊዮርጊስ፣በግብፅ ዋዲ ዳግላ እና አል አህሊ፣በቤልጂየሙ ሊርስ ክለብ፣በአልጀሪያው መውሊዲያ አለጀር እና በሲዳማ ቡና መጫዋት ችሏል፡፡

ሳላዲን ሰዒድ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከ31 ዓመታት በኋላ በአፍሪካ ዋንጫ በተሳተፈበት ወቅት የቡድኑ ወሳኝ ተጫዋች እንደነበር አይዘነጋም፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.