የቻይናው የውጭ ጉዳይ ቢሮ ዳይሬክተር ዋንግ ዪ አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይናው የውጭ ጉዳይ ቢሮ ዳይሬክተር ዋንግ ዪ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ዳይሬክተሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውላቸውል፡፡
ዳይሬክተሩ በቆይታቸው በኢትዮጵያ እና ቻይና ያለውን ዘርፈ ብዙ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ከከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ጋር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡