Fana: At a Speed of Life!

ከመገናኛ ወደ ላምበረት በሚወስደው መንገድ ለደረሰው ጉዳት የካሳ ክፍያ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፈው ሳምንት ጉዳት የደረሰበት ከመገናኛ ወደ ላምበረት የሚወስደው መንገድ ለደረሰበት ጉዳት የካሳ ክፍያ ተጠየቀ።

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን እንዳስታወቀው፤ እስራኤል ኤምባሲ አካባቢ የሚገኘው ዋና መንገድ ከ16 እስከ 18 ሜትር ቁፋሮ የተካሄደበት በመሆኑ ጉዳት ደርሶበታል።

መንገዱ የደረሰበት ጉዳት በባለሙያዎች ተጠንቶ የካሳ ክፍያ እንደተጠየቀበት ባለስልጣኑ አመልክቷል። መንገዱ ላይ ጉዳት በመድረሱ የትራፊክ እንቅስቃሴውን ማስተጓጎሉን ይታወሳል።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ቁፋሮው ሌሊት ላይ እንደሆነ እና በሰዓቱም ዝናብ እየጣለ እንደነበር ገልጸዋል።

በወቅቱ በአደጋው ምክንያት የትራፊክ መዘጋት በማጋጠሙ ህብረተሰቡ መጉላላቱንም ጠቅሰዋል።

በአደጋው የሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን ገልጸዋል።

ወቅቱ ክረምት እንደመሆኑ የሚካሄዱ የግንባታ ስራዎች በጥንቃቄ መካሄድ እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል።

በሲሳይ ጌትነት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.