Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በቀን 1 ሚሊየን ዳቦ የሚያመርቱ ፋብሪካዎች በነገው ዕለት ይመረቃሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ በቀን 1 ሚሊየን ዳቦ የሚያመርቱ የዳቦ ፋብሪካዎች እና የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከላት በነገው ዕለት ተመርቀው አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ ተገለፀ፡፡

በዚህም በነገው ዕለት ሶስት አዳዲስ የዳቦ ፋብሪካዎች እና ሁለት የምገባ ማዕከላት ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ይሆናሉ ነው የተባለው፡፡

የዳቦ ፋብሪካዎቹ በቀን ከ1 ሚሊየን በላይ ዳቦ የሚያመርቱ ሲሆን÷ በሙሉ አቅም ማምረት ሲጀምሩ በቀን እስከ 1 ነጥብ 6 ሚሊየን ዳቦ የማምረት አቅም ይኖራቸዋል መባሉን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በነገው ዕለት የሚመረቁት አዲስ የተገነቡት ሁለት የምገባ ማዕከላት የከተማዋን የምገባ ማእከላትን ቁጥር 19 እንደሚያደርሱት ተገልጿል፡፡

ዳቦ ፋብሪካዎቹ እና የምገባ ማዕከላቱ የህዝቡን የኑሮ ሸክም ለማቅለል ከተማ አስተዳደሩ በክረምት የበጎ ፈቃድ ስራው ባለሀብቶችና ተቋማት ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ባደረገው ጥረት የተሰሩ ናቸው ነው የተባለው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.