Fana: At a Speed of Life!

ፌዴራል የሱፐርቪዥን ቡድን አባላት ከከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ጋር የማጠቃለያ ውይይት አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ አመራር የሆኑ የሱፐርቪዢን ቡድን አባላት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ጋር የማጠቃለያ ውይይት አካሄዱ፡፡

ቡድኑ ለተከታታይ 10 ቀናት በተለያዩ የከተማዋ ክፍለ ከተሞች ፣ ወረዳዎች እንዲሁም እስከ ቤተሰብ ድረስ በመውረድ ተዘዋውረው የመስክ ምልከታ ማድረጉ ተጠቅሷል፡፡

በጉብኝታቸው ወቅትም በርካታ በተሞክሮ የሚወሰዱ ጥንካሬዎቻን እንዲሁም መሻሻል በሚገባቸው ውስንነቶች ላይ ግብረ መልስ ሰጥተዋል ነው የተባለው፡፡

አመራሮቹ በቆይታቸው ወቅት ለሰጡት ገንቢ አስተያየትና ድጋፍ የከተማ የአስተዳደሩ ከፍ ያለ ምስጋና ማቅረቡን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽኅፈት ቤት መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.