ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለጋዜጠኛ መአዛ ብሩ እና ለግብርና ባለሙያው ጌሪት ሆትላንድ የክብር ዶክትሬት ሰጠ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 15 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለጋዜጠኛ መአዛ ብሩ እና ለግብርና ባለሙያው ጌሪት ሆትላንድ የክብር ዶክትሬት ሰጠ።
ዩኒቨርሲቲው ጋዜጠኛ መአዛ ብሩ በጋዜጠኝነት ሙያ ላበረከተችው አስተዋጽኦ የክብር ዶክትሬት መስጠቱን አስታውቋል።
ጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ በሙያዋ ያበረከተችው ላቅ ያለ አስተዋጽኦና ተፅዕኖ ፈጣሪነቷ ለዚህ ክብር እንዳበቃትም ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።
በተመሳሳይም በግብርና ልማት ዘርፍ የ35 ዓመታት ልምድ ያላቸውና ባለፉት 11 ዓመታት በዘርፉ አስተዋጽኦ እያደረጉ ለሚገኙት ጌሪት ሆትላንድ የክብር ዶክትሬት መስጠቱን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል።
በተለይም በአነስተኛ ማሳ የሚያመርቱ አርሶ አደሮች ምርታማነትን በማሳደግ ኑሯቸው እንዲሻሻል ብዙ መስራታቸው ተጠቅሷል።
የክብር ዶክትሬቱን ዩኒቨርሲቲው በዛሬው እለት በበተለያዩ መርሐ ግብሮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ባስመረቀበት ወቅት አበርክቷል።