Fana: At a Speed of Life!

ተመራቂዎች ድህነትን በዕውቀት ለማሸነፍ መትጋት አለባችሁ – ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ተመራቂዎች ድህነትን በዕውቀት ለማሸነፍ መትጋት አለባችሁ ሲሉ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ተናገሩ።

ዛሬ በተለያዩ መርሃ-ግብሮች ያሰለጠናቸውን ከ1 ሺህ 400 በላይ ተማሪዎችን ያስመረቀው የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፤ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ አቶ ታቦር ዋሚ እንዲሁም አቶ ዘገየ አስፋው ላበረከቱት አስተዋጽኦ የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል።

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በትምህርትና በሰብዓዊ ልማት ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋጽኦ የክብር ዶክትሬቱ እንደተሰጣቸውም በወቅቱ ተገልጿል።

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በስነ-ስርአቱ ላይ፤ ተመራቂዎች ድህነትን በዕውቀት ለማሸነፍ መትጋት ይገባችኋ ብለዋል።

የትምህርት እና የጤና መሰረተ ልማቶችን ማሻሻል ድህነትን ለማሸነፍ ወሳኝ ሚና እንዳላቸው ገልጸው፤ “ኢትዮጵያውያን ከተባበርን የብዙዎችን እንባ ማበስ፣ ለችግረኞች ተስፋ መሆንና ሀገራችንን መገንባት እንችላለን” ብለዋል።

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ተመራቂዎች በቆይታቸው ያገኙትን ዕውቀት ለሀገር ልማት ማዋል እንደሚገባቸው ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.