Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከአሜሪካ ኮንግረስ አባልና ከኢትዮጵያ-አሜሪካ ካውከስ ሊቀ መንበር ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከአሜሪካ ኮንግረስ አባልና ከኢትዮጵያ-አሜሪካ ካውከስ ሊቀ መንበር ጆን ጋራሜንዲ ጋር በአሜሪካ ውይይት አደረጉ።

የኮንግረስ አባሉ ጋራሜንዲ ከኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ጋር ላላቸው ቀጣይነት ያለው ወዳጅነት አመስግነዋል፡፡

በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አፈጻጸም ሂደት፣ የሰላም ማጠናከር ስራዎች፣ በኢትዮጵያ ከግጭት በኋላ የማገገሚያ እና መልሶ ማቋቋም ስራዎችን መደገፍ እንደሚያስፈልግም ነው የገለጹት።

በተጨማሪም በሀገራዊ፣ ክልላዊ እና ዓለም አቀፍ የጋራ ጉዳዮች ላይም መምከራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ጋራሜንዲ፥ ኢትዮጵያ ትልቅ ስኬት ማስመዝገቧን አድንቀውም ፥ በኢትዮጵያና አሜሪካ መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለማደስ ጠንካራ ተሟጋች ሆነው እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.