Fana: At a Speed of Life!

በደብረ ማርቆስ በትራፊክ አደጋ የ5 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደብረ ማርቆስ ከተማ ተድላ ጓሉ ክፍለከተማ ቀበሌ 18 እነችፎ ቡልቸድ አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአምስት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

ትናንት ምሽት 12፡00 ላይ በደረሰው የትራፊክ አደጋ÷ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል መባሉን የምሥራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

አደጋው የደረሰው÷ ከደብረ ማርቆስ ወደ መካልያ እና ከአዲስ አበባ ወደ ባሕርዳር ይጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች በመጋጨታቸው ነው፡፡

በዚህም ከደብረ ማርቆስ ወደ መካልያ ይጓዝ በነበረው ተሸከርካሪ ውስጥ የነበሩ 3 እንዲሁም ከአዲስ አበባ ወደ ባሕርዳር ይጓዝ ከነበረው ደግሞ 2 ሰዎች ወዲያውኑ ሕይወታቸው ማለፉ ነው የተገለጸው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.