Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል ከ1 ነጥብ 6 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት በበቆሎ ሰብል ተሸፈነ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በያዝነው የመኸር እርሻ ወቅት በኦሮሚያ ክልል ከ1 ነጥብ 6 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት በበቆሎ ሰብል መሸፈኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ፡፡

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ስንመኘው የኖርነው ተስፋ ምን ያህል ወደ እውነት እንደተቀየረ አይተናል ብለዋል፡፡

የተጀመሩ ሁሉም የግብርና ኢኒሼቲቮች በክልሉ የገጠር ኢኮኖሚ ውስጥ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ፣ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በመተካት፣ ኤክስፖርትን በማሳደግ እና የስራ ዕድል በመፍጠር የኢትዮጵያን ግብርና ለውጥ እያረጋገጡ ስለመሆኑም ጠቁመዋል፡፡

የወደፊቷ ኢትዮጵያ ተስፋ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ዕውን ይሆናል ሲሉም ገልጸዋል ርዕሰ መስተዳድሩ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.