Fana: At a Speed of Life!

ደቡብ ኮሪያ በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ እርዳታ የሚውል የ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ደቡብ ኮሪያ በኢትዮጵያ ለተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ የሚውል ተጨማሪ የ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አድርጋለች፡፡

ድጋፉ በዓለም የምግብ ፕሮግራም፣ በዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማህበር፣ በተመድ የህጻናት መርጃ ድርጅት እና በተመድ የሰብዓዊ መብቶች ም/ቤት አማካኝነት የሚሰራጭ ነው ተብሏል፡፡

ደቡብ ኮሪያ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ እርዳታ ለሚሹ ዜጎች አስፈጊውን ድጋፍ ለማድረግ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗም ተገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ እርዳታ እያሰራጩ ከሚገኙ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በቅንጅት እንደምትሰራ መገለጹንም በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

ደቡብ ኮሪያ በተያዘው የፈረንጆች ዓመት በኢትዮጵያ በተለያዩ ምክንያቶች ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች 10 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶላር ድጋፋ ማድረጓ ተጠቁሟል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.