Fana: At a Speed of Life!

ለአጠቃላይ የኢኮኖሚ እድገት አዲስና ጠንካራ ዓለም አቀፍ የግብርና የፋይናንስ ሞዴል አስፈላጊ ነው- ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለምግብ ዋስትና፣ ለስራ እድል ፈጠራ ብሎም ለአጠቃላይ የኢኮኖሚ እድገት አዲስ እና ጠንካራ ዓለም አቀፍ የግብርና የፋይናንስ ሞዴል አስፈላጊ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብ ስርዓት ጉባኤ ላይ መሳተፋቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

በጉባኤው ለምግብ ዋስትና፣ ለስራ እድል ፈጠራ ብሎም ለአጠቃላይ የኢኮኖሚ እድገት አዲስ እና ጠንካራ ዓለም አቀፍ የግብርና የፋይናንስ ሞዴል አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በኢትዮጵያ ከፖሊሲ እና ስትራቴጂዎች ባለፈ የግብርና ልማትን ለማጎልበት አቅምን ማሳደግ እና በምግብ ራስን መቻልን ለማረጋገጥ ግቦችን ይዛ እየሰራች መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም የአየር ንብረት ለውጥን የመዋጋት ግብ ይዛ በርካታ ጅምር ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.