ስፓርት

ንግድ ባንክ በ2015 ዓ.ም ውጤት ላስመዘገቡ ስፖርተኞች ሽልማት አበረከተ

By Mikias Ayele

July 24, 2023

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2015 ዓ.ም በተለያዩ የስፖርት ዘርፎች የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ስፖርተኞች እና ባለሙያዎች የእውቅና እና የማበረታቻ ሽልማት አበርክቷል።

ባንኩ ባለፈው ዓመት በተካሄዱ የአትሌቲክስ፣ እግርኳስና የጠረጴዛ ቴንስ ውድድሮች በድምሩ 38 ዋንጫ ማንሳት የቻለ ሲሆን÷ ለዚህ ውጤት መገኘት አስተዋጽኦ ለነበራቸው ስፖርተኞች በዛሬው ዕለት ሽልማት አበርክቷል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የስፖርት ማህበር ፕሬዚዳንት ኤፍሬም መኩሪያ ባንኩ በስፖርቱ መስክ ሰኬታማ የውድድር ዘመን ማሳለፉን ገልፀው÷ ክለቡ በሀገሪቱ ስፖርት ላይ ትልቅ አሻራ ማኖሩን አንስተዋል።

በሴቶች እግር ኳስ የኢትዮጵያ  ንግድ ባንክ ሁሌም ከፊት ሆኖ የሚመራ መሆኑን ጠቁመው÷ የሴቶች ቡድን በሴካፋ ዞን የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ውጤታማ ለመሆን እንደሚሰራ ተናግረዋል ።

በወርቅነህ ጋሻሁን