Fana: At a Speed of Life!

ፓኪስታን በንግዱ ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር እንደምትሰራ አመላከተች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፓኪስታን በንግድና ምጣኔ ሐብት ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር እንደምትሰራ አመላከተች፡፡

የፓኪስታኑ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሪፍ አልቪ ÷ በኢትዮጵያ የፓኪስታን አምባሳደር ሆነው ለተሾሙት ሚአን አቲፍ ሻሪፍ በጉዳዩ ላይ አበክረው እንዲሰሩ መመሪያ መሥጠታቸውን ዘ ኔሽን ዘግቧል፡፡

ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሪፍ አልቪ ÷ የሁለቱ ሀገራት የንግዱ ዘርፍ ማኅበረሰቦች ግንኙነት እንዲጠናከርም ምኅዳሩን በማመቻቸት ረገድ አምባሳደሩ የሚጠበቅባቸውን ሁሉ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

አምባሳደሩ የፓኪስታንን ምርቶች ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ በውጭ ንግድ ላይ ከተሰማሩ የኢትዮጵያ ነጋዴዎች ጋር ተቀራርበው እንዲመክሩም ነግረዋቸዋል።

ፕሬዚዳንቱ በትምህርቱ ዘርፍ “ፓኪስታን ዩኒቨርሲቲ” እና “አላማ ኢቅባል ኦፕን ዩኒቨርሲቲ” የተባሉት ሁለት ከፍተኛ ተቋማት በበይነ-መረብ ለኢትዮጵያውያን ተደራሽ መሆን እንደሚፈልጉ መጠቆማቸውንም ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም በዘርፉ ያለውን የሀገራቱን ፍላጎት ለማርካትና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር አምባሳደሩ አበክረው እንዲሰሩ መመሪያ ሰጥተዋል።

ፓኪስታን ወጣት ኢትዮጵያውያን ዲፕሎማቶችን ተቀብላ በውጭ ግንኙነት ለማሰልጠን እንዲሁም በባንኩ ዘርፍ ላይ የውጭ ዕድል በመሥጠት የሁለትዮሽ ግንኙነቷን የበለጠ ለማጠናከር ያላቸውን ፍላጎትም ለአምባሳደሩ ነግረው በጉዳዩ ላይ እንዲሠሩ አሳስበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.