Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ከስዊዘርላንድ ጋር ያላትን የኢኮኖሚ ትብብር ታጠናክራለች – ለሊሴ ነሜ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በምጣኔ ሐብቱ ዘርፍ ኢትዮጵያ ከስዊዘርላንድ ጋር ያላትን ትብብር ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ (ኢ/ር) ገለጹ።

ኮሚሽነሯ በኢትዮጵያ ከስዊዘርላድ አምባሳደር ታማራ ሞና ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ ስላሉ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች አስረድተዋል፡፡

በዘርፉ ያለውን እምቅ አቅም በመጠቀም ሀገራቱ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር በሚችሉባቸው ሁኔታዎች ላይ መምከራቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ሁለቱ ሀገራት ከኢኮኖሚው በተጨማሪ በልማት ፣ በፈጠራ ሥራዎች ፣ በምርምር ፣ በትምህርት እና በሰብዓዊ ጉዳዮች መልካም ግንኙነት እንዳላቸው ተገልጿል።

ኢትዮጵያ እና ስዊዘርላንድ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የጀመሩት በፈረንጆቹ 1933 ሲሆን ስዊዘርላንድ ኤምባሲዋን በኢትዮጵያ የከፈተችው ደግሞ በፈረንጆቹ 1962 በአዲስ አበባ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.