የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችንና አዋጆችን በማጽደቅ ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ሲያካሂድ የቆየዉን 16ኛ መደበኛ ጉባኤ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤን ጨምሮ የተለያዩ ሹመቶችንና አዋጆችን በማጽደቅ ተጠናቋል ።
ምክር ቤቱ ሲያካሂድ በቆየው መደበኛ ጉባኤ በቀረቡ አጀንዳዎችን ላይ በመምከር ውሳኔዎችን አስተላልፏል።
በዛሬው ውሎውም ለምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤነት በእጩነት የቀረቡትን ተመስገን ዲሳሳ(ዶ/ር)ን ዋና አፈ ጉባኤ አድርጎ ሹሟል።
በተጨማሪም በክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ለተቋማት የስራ ሀላፊነት ለጉባኤዉ የቀረቡ 11 ተሿሚዎችንና ሽግሽጎችን በመመርመር ሹመታቸውን በሙሉ ድምጽ ማፅደቁን ከክልሉ መገናኛ ብዙኃን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ጉባኤው በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀረቡ የ18 የተለያዩ ፍርድ ቤት ዳኞችን ሹመት ተቀብሎ ያጸደቀ ሲሆን÷ በተጨማሪ የክልሉ አስፈጻሚ አካላት ስልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን በቀረበዉ አዋጅ ላይና በሌሎች አዋጆች ላይ በመወያየት ወስኗል።