በአቶ ገብረመስቀል ጫላ የተመራ ልዑክ በጄኔቫ የስራ ጉብኝት እያደረገ ነው
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ገብረመስቀል ጫላ የተመራ ልዑክ በስዊዘርላንድ ጄኔቫ የስራ ጉብኝት እያደረገ ነው፡፡
የልዑካን ቡድኑ አባላት በስዊዘርላንድ ቆይታቸው ጄኔቫ የሚገኘውን የዓለም የንግድ ጽሕፈት ቤት ጎብኝተዋል፡፡
የጉብኝት መርሐ ግብሩ ኢትዮጵያ በዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት እያካሄደች ላለው እንቅስቃሴ አጋዥ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
ልዑኩ ከዓለም የንግድ ድርጅት ጽ/ቤት ከፍተኛ ሃላፊዎች፣ ከተመረጡ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ሀገራት እና ድርጅቱን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ከሚገኙ ሀገራት ጋር መምከሩን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡