ቤቶች ኮርፖሬሽን 2 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ሰበሰበ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በበጀት ዓመቱ 2 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡
የኮርፖሬሽኑ የ2015 ዓ.ም አፈጻጸም እና የ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት ዕቅድ ተገምግሟል፡፡
በበጀት ዓመቱ በቤት አስተዳደር፣ በቤት ልማት፣ በኮንስትራክሽን ግብዓት አቅርቦት፣ በአገልግሎት ዘርፍ እና ስትራቴጂክ የሥራ ክፍሎች የተከናወኑ ሥራዎች አበረታች መሆናቸውን የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል ተናግረዋል፡፡
የገቢ አማራጮችን በማስፋት ተቋሙ ያለውን ገቢ በአግባቡ መሰብሰብ መቻሉን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡
አጠቃላይ የኮርፖሬሽኑ ሀብትም አሁን ላይ ከ260 ቢሊየን ብር በላይ መድረሱን ተመላክቷል፡፡