Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በግብጽ አዲስ እየተገነባ ያለውን የካይሮ ከተማ ጎበኘ

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከተለያዩ ከተሞች እና ተቋማት የተውጣጣ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በግብጽ አዲስ እየተገነባ ያለውን የካይሮ ከተማ ጎብኝቷል፡፡

ልዑኩ በጉብኝቱ ጥንታዊነትን ከዘመናዊነት፤ ገጠርን ከከተማ አስማምቶ ለማደግ የተከናወኑ ተግባራትን መመልከቱ ተገልጿል፡፡

በጉብኝቱ ወቅት ከካይሮ ከተማ አስተዳደር ጋር ከተሞችን በማዘመን፣ ወቅቱን የዋጀ የከተማ እና የመሠረተ ልማት ግንባታን እንዲሁም የተጨናነቁ የከተማ አካባቢዎችን ስለማስተካከል በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል።

ኢትዮጵያና ግብጽ በባህል፣ በታሪክና በሌሎች ተቀራራቢነት ያላቸው በመሆኑ ልዑኩ ያገኘው ልምድ በየከተሞቹ ሊተገበሩ የሚችሉ መሆናቸውን አባላቱ ገልጸዋል።

ጉብኝቱ ሐምሌ 6 ቀን 2015 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በግብጽ ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ የተከናወነ ነው ተብሏል።

በጉብኝት መርሐ ግብሩ የፌዴራል አመራሮች፣ የአዲስ አበባ፣ የአዳማ፣ የባሕር ዳር እና የሐዋሳ ከንቲባዎች መሳተፋቸው ታውቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.