የሐረሪ ብሔራዊ ጉባዔ መካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ብሔራዊ ጉባዔ 6ተኛ ዙር 2ኛ ዓመት 2ኛ መደበኛ ጉባዔውን ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል፡፡
በጉባዔው ላይ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፣ የሐረሪ ብሔራዊ ጉባዔ አፈ-ጉባዔ ሙህየዲን አሕመድ፣ ምክትል አፈ -ጉባዔ ዚነት ዩሱፍን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
ጉባዔው የ6ተኛ ዙር 2ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባዔ ቃለ-ጉባዔ እንደሚጸድቅ ይጠበቃል መባሉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡
በባሕል፣ ቅርስና ቱሪዝም እንዲሁም በትምህርት ዘርፍ በ2015 ዓ.ም የተከናወኑ ተግባራትን አፈጻጸም እና የ2016 ዕቅድን በመገመገም እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል ተብሏል፡፡
በተጨማሪም የተሻሻለው የጉባዔው የአሠራር እና አባላት ሥነ- ምግባር አዋጅ ለጉባዔው ቀርቦ በአባላቱ ውይይት ይጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም ነው የተመለከተው፡፡