ኢትዮጵያና የአለም ባንክ የ400 ሚሊየን ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና የአለም ባንክ የ400 ሚሊየን ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
የአለም ባንክ ለኢትዮጵያ ለሰው ሀብት ልማት አገልግሎት የሚውል የ400 ሚሊየን ዶላር (የ21 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር) የፋይናንስ ድጋፍ ለማድረግ የተስማማ ሲሆን ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴና ሚስተር ኦስማን ዲዮን ፈርመውታል፡፡
የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነቱ ስነ-ስርዓቱ የተካሄደው በበይነ መረብ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በስምምነቱ ከተፈረመው 400 ሚሊየን ዶላር ውስጥ 350 ሚሊየን ዶላሩ የልማት ድጋፍ ሲሆን 50 ሚሊየን ዶላሩ ደግሞ ብድር መሆኑን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ድጋፉ ለሰው ሀብት ልማት ማለትም የትምህርትን ጥራትንና ውጤታማነትን ለማሻሻልና የስርዓተ ምግብን አገልግሎት ለማጎልበት የሚውል ሲሆን ከአገልግሎቱም በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ልጃገረዶችና ታዳጊ ወጣቶች ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል፡፡
የሰው ሀብት ልማት አገልግሎቱ በግጭትና ድርቅ የተጎዱ አካባቢዎችን የሚያካትት ሲሆን የማህበራዊ አገልግሎቶች አሰጣጥን ለማጠናከርና ተጠያቂነትን ለማስፈንም አስተዋጽዖ እንዳለው ታውቋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!